32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ ልዩነት
32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ ልዩነት እንደምናችሁ ወዳጆቼ ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት ይዘ ቀርቤለሁ ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ(አፕግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትዌር ለመወሰን ያግዛል፡፡ የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት በሚል የሚከፈል ሲሆን የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም አይነት እክል የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌሮች ይወስኑታል፡፡ 32 ቢት ፕሮሰሰር፦ 32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ የምገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና ኤኤምዲ እየሰሩ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ ማክሮሶፍ ዊንዶ 95፣ 98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡ 32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የማንችል ሲሆን ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን የሚችለው 32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር፦ 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961 አካባቢ አይቢኤም IBM 7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም እስከ 2000 ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ አልነበረም በማክሮሶፍት 64 ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ አቀረበ በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64 ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገ...