32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ ልዩነት

32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ ልዩነት

እንደምናችሁ ወዳጆቼ ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት ይዘ ቀርቤለሁ ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ(አፕግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትዌር ለመወሰን ያግዛል፡፡
የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት በሚል የሚከፈል ሲሆን የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም አይነት እክል የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌሮች ይወስኑታል፡፡
32 ቢት ፕሮሰሰር፦
32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ የምገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና ኤኤምዲ እየሰሩ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡
ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ ማክሮሶፍ ዊንዶ 95፣ 98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡
32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የማንችል ሲሆን ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን የሚችለው 32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡

64 ቢት ፕሮሰሰር፦
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961 አካባቢ አይቢኤም IBM 7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም እስከ 2000 ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ አልነበረም በማክሮሶፍት 64 ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ አቀረበ በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64 ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡

ማስታወሻ
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 16 ቢት ተብለው የተሰሩ ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች የማይሰራ ሲሆን ብዙ 32 ቢት የሆኑ ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን ሲስተም ላይ የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatible አይደሉም)
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት አንዱ ልዩነታቸው ሲሆን 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad core፣ በsix core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ ነው፡፡
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው በኮምፒውተሩ ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም የሚያስችል ሲሆን 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር ከ4GB በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣ ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64 ቢት እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64 ቢት እንዲሆኑ የተገደዱ ሲሆን ይሄም የፕሮሰሰር አምራቾች 64 ቢት ፕሮሰሰር በስፋት ወደገበያ እያቀረቡ ነው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የኢንተርኔት ፍጥነት መጨመሪያ መላዎች

እንዴት የስልክ ቁጥርዎን መደበቅ ይችላሉ?

የሞባይል ባትሪንእድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮች