የስልክ የኢንተርኔት ዋጋ ፍጆታን እንዴት መቀነስ ይቻላል?

የስልክ የኢንተርኔት ዋጋ ፍጆታን እንዴት መቀነስ ይቻላል?
ለአንድሮይድ ስልኮዎት ኢንተርኔት ሲጠቀሙ በዛ ያለ ገንዘብ እየወሰደ ከተማረሩ የሚከተለውን ያድርጉ።
በአንድሮይድ ስልኮች ኢንተርኔት ስንጠቀም ገንዘብ እንዳይወስድብን ለማድረግ የሚረዱን የተለያዩ ዘዴዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የምንጠቀመውን የዳታ መጠን መወሰን አንዱ ነው።
ይህንን ለማድረግም በመጀመሪያ የሞባይላችን ሴቲንግ ውስጥ በመግባት ሞባይል ዳታ የሚለውን ስንጫን ከሚመጡልን ውስጥ ሊሚት የሚለውን በመጫን ማስተካከል / Dta usage- Mobile Data on- Set Mobile Data limit/ ማድረግ። ይህንን በማድረግ ምን ያክል ሜጋ ባይት ኢንተርኔት መጠቀም እንዳልብን በማድረግ የኢንተርኔት ወጪያችንን መቆጠብ እንችላለን።
ሌላኛው የኢንተርኔት የገንዘብ ፍጆታ መቀነሻ መንገድ ተብሎ የተቀመጠው ደግሞ በስልካችን ላይ ያሉ እና ሁሌም የማንጠቀምባቸውን መተግበሪያ / አፕሊኬሽኖችን መዝጋት ነው። በስልካችን ላይ ያሉ መተግበሪያዎች ሞባይል ዳታችንን ስንከፍት እራሳቸውን አፕዴት እያደረጉ የኢንተርኔት የገንዘብ ፍጆታችንን ከፍ ሊያደርጉብን ይችላሉ። ስለዚህም እነዚህን ሁሌም የማንጠቀምባቸውን መተግበሪያዎች በመዝጋትም የኢንተርኔት ወጪያቸንን መቀነስ እንችላለን።
ይህንን ለማድረግም መጀመሪያ ሴቲንግ ውስጥ በመግባት / Data usage / የሚለውን ስንከፍት በስልካችን ላይ ያሉ እያንዳንዳቸው መተግበሪያዎች ምን ያክል ሜጋ ባይት ኢንተርኔት እንደተጠቀሙ ወደ ታች ይዘረዝርልናል።
በመቀጠልም / Data usage / ውስጥ የተዘረዘሩትን ሁሉንም መተግበሪያዎች በየተራ እየከፈትን ከታች የሚመጣልንን ሪስትሪክት ባግራውንድ ዳታ /Setting- Data usage- Oppen apps- Restrict background Data/ የሚለውን በመጫን የኢንተርኔት ወጪያችንን መቀነስ እንችላለን።
ይህንን ዘዴ የምንጠቀም ከሆነ አዲስ መተግበሪያ /አፕሊኬሽን በጫን ቁጥር እየገባን ዳታውን መዝጋት ይኖርብናል።
ለወዳጆ ሼር ማድረግዎን አይርሱ
-------------------------

Comments

Popular posts from this blog

የኢንተርኔት ፍጥነት መጨመሪያ መላዎች

እንዴት የስልክ ቁጥርዎን መደበቅ ይችላሉ?

የሞባይል ባትሪንእድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮች