እንዴት የስልክ ቁጥርዎን መደበቅ ይችላሉ?

እንዴት የስልክ ቁጥርዎን መደበቅ ይችላሉ?
................................................................
የሞባይል ስልክ ቁጥርዎ ድብቅ እንዲሆን ይፈልጋሉ? የእርስዎ ቁጥር ድብቅ/የማይታይ እንዲሆን የሚፈልጉበት ብዙ ምክንያቶች ሊኖር ይችላሉ ፡፡ ስለዚህ እርስዎ የስልኩ ባለቤት ስለሆኑ የፈለጉትን የማድረግ መብትዎ ነው፡፡ ውጤቱ ጊዜያዊ ወይም ቋሚ ሊሆን ቢችልም ተመሳሳዩን ግብ ለማሳካት የተለያዩ መንገዶች አሉ፡፡
በዚህ በምነግራችሁ ሂደት ውስጥ በሚደውሉበት ጊዜ የስልክ ቁጥር መደበቅ ስለሆነ ሶስት የተለያዩ መንገዶችን እጠቁማለሁ የቀለለውን እና የተሻለውን የሚስማማውን መጠቀም ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ: ምንም እንኳን ስደውሉ ስልክ ቁጥሩ ድብቅ ቢሆንም የድንገተኛ አደጋ ቁጥሮችእንደ 911 አይታገድም
መንገድ 1: ለመደወል ቅድመ ቅጥያ ይጠቀሙ
በአብዛኛው አገሮች ውስጥ ለመደወል የሚፈልጓቸውን ቁጥሮች መጀመሪያ ላይ ኮድ ማስገባት የሚያስፈልግ ሲሆን በሚደውሉበት ጊዜ ቁጥሩ በተቀባዩ ስልክ ላይ አይታይም፡፡
ኮዱ ከአገር ወደ አገር እንዲሁም የስልክ ካምፓኒዎች የሚለያይ በመሆኑ ትክክለኛውን ኮድ ማግኘት ያስፈልጋል ይሁን እንጂ በአብዛኞቹ አገሮች ቅድመ ቅጥያ ኮድ * 67፣ # 37 # እና * 37 # ይሰራል፡፡ ስለዚህ እርስዎ የሚኖሩበትን አገር እንዲሁም የያዙትን ስልክ ካምፓኒ ኮድ የማያውቁት ከሆነ እነዚህን መጀመሪያ ይሞክሩ
እርስዎ ማድረግ የሚጠበቅብዎት ከመደወልዎ በፊት ከላይ ያሉትን አንዱን ኮድ አስቀድመው የሚደውሉለትን ሰው ቁጥር በመጨመር መደወል ነው፡፡
ለምሳሌ፡- * 67XXXXXXXXXX
መጀመሪያ የትኛው ኮድ እንደሚሠራልዎ ይሞክሩ አስተያየትዎን ይስጡን
መንገድ 2፡ በሞባይል ስልኩ ሴቲንግ ላይ ያለውን ቅንብሮች ይጠቀሙ
ዛሬ አብዛኞቹ ስልኮች በስልኩ ቅንጅቶች ውስጥ የተካተቱ የደዋይ መታወቂያ ባህሪያትን ይዘው ይመጣሉ፡፡ በበርካታ ስልኮች ላይ ወደ ሴቲንግ አማራጮች ላይ በመሄድ ሊያቀናብሩ ይችላሉ( ሂደቱ ከስልክ / ስልክ ሊለያይ ይችላል)
ለምሳሌ በ Android KitKat 4.4 ላይ ወደ ሴቲንግ ቅንጅቶች መሄድና መክፈት Settings – Call- Additional Settings- Caller ID ከዛም “Hide Number” የሚለውን እንምረጥ፡፡ በዚህ ሂደት የስልክ ቁጥርዎ ለተቀባዩ “Private number” በሚል ይታያል፡፡
ይሁን እንጂ ቁጥርዎ በሚታወቅባቸው ቦታዎች ላይ አስፈላጊ በሚሆንባቸው ጊዜያት በማንኛውም ጊዜ ሲፈልጉ ከላይ የተጠቀሱትን ተመሳሳይ ሂደት በመከተል “Show number” የሚለውን ይምረጡ
ማስታወሻ- አንዳንድ ቴሌኮም ድርጂቶች ይሄን ሰርቪስ የማይፈቅዱ/ክፍት ላያደርጉት ይችላሉ በዚህ መንገድ መጀመሪያ እንደሚሰራ ይሞክሩት ካልሆነ አገልግሎት የሚያገኙበት ቴሌኮም ይሄን ሰርቪስ እንዲሰራ አክትቬት/ክፍት ማድረግ እንዳለበትይጠይቁ
መንገድ 3: የሞበይል ስልክ መስመር ሻጩን ድርጂት ያነጋግሩ
የሞባይል ስልክ ቁጥርዎ እርሶ ለፈለጉት ሰው ብቻ መደወል የሚችሉ ሲሆን ቁጥሩ በጭራሽ አይታይም ይሄ አገልግሎት ሁልግዜ በቆሚነት የሚጠቀሙበት ሲሆን እርስዎ ሙሉ በሙሉ ማንነትዎን ለመደበቅ የሚፈልጉ ከሆነ ጥሩ ምርጫ ነው፡፡
ነገር ግን ይህን አገልግሎት በነጻ ሊገኝ አይችልም እንደ መስመር ሻጩ ድርጂት የክፍያ ታሪፍ መሰረት ክፍያ ያስከፍላል፡፡
ያለዎትን አስተያየት ይስጡን የናንተ አስተያየት የኛ ብርታት ነው

Comments

  1. ስለዚ በኛ ሀገር ቴሌ ይሰራል አይሰራም ?

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular posts from this blog

የኢንተርኔት ፍጥነት መጨመሪያ መላዎች

የሞባይል ባትሪንእድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮች