የፌስቡክ ሜሴንጀር ወርሃዊ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ደረሰ

የፌስቡክ ሜሴንጀር ወርሃዊ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር 1 ነጥብ 3 ቢሊየን መድረሱን ኩባንያው አስታወቀ።
ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር የፌስቡክ ሜሴንጀር ወርሃዊ ተጠቃሚዎች ቁጥር 1 ነጥብ 2 ቢሊየን መድረሱ ይታወሳል።
የተጠቃሚዎቹ ቁጥር 1 ቢሊየን የደረሰው ደግሞ በፈረንጆቹ 2016 ሃምሌ ወር ነበር።
በሜሴንጀር የሚሰጡ አገልግሎቶች ማራኪና ቀልጣፋ እንዲሆኑ የቪዲዮ መልዕክቶች ምላሽም ፈጣን እንዲሆን እየሰራን ነው ብሏል ኩባንያው።
ከዚህም ባሻገር ለአጠቃቀም ምቹ የሆነውን ፌስቡክ ሊት የተባለ መተግበሪያን ለዓለም በማስተዋወቅ ደንበኞች እንዲጠቀሙ ማድረግ ከተጀመር ሰንበትበት ማለቱንም አስታውሷል።
አሁን የፌስቡክ ሜሴንጀር ወርሃዊ ደንበኞች 1 ነጥብ 3 ቢሊየን መድረሱ፥ ይህን ቁጥር ባሳለፍነው ሃምሌ ወር ከደረሰበት ዋትሰአፕ ጋር እኩል እንዲቀመጥ አስችሎታል።
ሁለቱ የፌስቡክ ኩባንያ ንብረቶች በዓለም ላይ ካሉ የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎች ሁሉ ተመራጭና ግዙፍ ደንበኛ ያላቸው ሆነዋል።
የፌስቡክ ሜሴንጀርና የዋትሰአፕ ተጠቃሚዎች ቁጥር እያደገ መምጣቱን ተከትሎ፥ በሁለቱም የመልዕክት መለዋወጫዎች የማስታወቂያ አገልግሎቶችን ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል።
በዋትስአፕ ላይ ከነሃሴ ወር ጀምሮ የተረጋገጡ የቢዝነስ አድራሻዎች ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ ነው።
በፌስቡክ ሜሴንጀር ደግሞ ካሳለፍነው ሃምሌ ወር ጀምሮ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ ተግባራዊ ተደርጓል።

Comments

Popular posts from this blog

የኢንተርኔት ፍጥነት መጨመሪያ መላዎች

እንዴት የስልክ ቁጥርዎን መደበቅ ይችላሉ?

የሞባይል ባትሪንእድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮች