የሞባይል ቀፎዎች እና ሌሎች በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሳሪያዎን ያስመዝግቡ
ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ቀፎዎችን እና ሌሎች በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች መለያ ቁጥር ምዝገባ በማድረግ ተመሳስለው የተሰሩ እና ደረጃቸውን ያልጠበቁ እንዲሁም ከደንበኞች እጅ የጠፉ/የተሰረቁ መሳሪያዎች በኩባንያው ኔትወርክ ላይ አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግ የሚያስችል አዲስ አሰራር በስራ ላይ ለማዋል ዝግጀቱን አጠናቀቀ፡፡
ምዝገባው ለደንበኞች የሚሰጣቸው ጠቀሜታዎች
• ደረጃቸውን ባልጠበቁና ተመሳስለው በተሰሩ የሞባይል ቀፎዎች እና ሌሎች በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሳሪያዎች ምክንያት ሊያጋጥም የሚችለውን የአገልግሎት ጥራት እና በጤና ላይ ሊያደርሱ የሚችለውን ችግር ማስወገድ፡፡
• በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች በስርቆትም ሆነ በሌላ ምክንያት ከደንበኞች እጅ ሲጠፉ ደንበኞች 994 ላይ በመደወል በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ቀፎው የቴሌኮም አገልግሎት እንዳይሰጥ በማድረግ በደንበኞች ላይ ሊከሰት የሚችለውን የቀፎ ስርቆት ለመቀነስ ይረዳል፡፡

የምዝገባው ጊዜ
• እስከ መስከረም 7 ቀን 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ አገልግሎት እየሠጡ የማይገኙ ቀፎዎች ካሉ ሲም ካርድ አስገብቶ በማብራት እና በመጠቀም ማስመዝገብ ይቻላል፡፡

ምዝገባው የሚመለከታቸው የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች
• ሞባይል ስልክ፣ዶንግል፣ዋይፋይ ራውተር፣ታብሌት፣የካሽ ሬጅስተር ማሽን እና ሌሎችም ሲም ካርድ የሚቀበሉ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች

የምዝገባ ሁኔታ
• ምዝገባው በሲስተም አማካኝነት ከማዕከል የሚደረግ በመሆኑ ደንበኞች ወደ ኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል መምጣት ሳይጠበቅባቸው ባሉበት ቦታ ሆነው ሲም ካርድ አስገብተው በማብራት እና በመጠቀም ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡

ከምዝገባ በኋላስ?
• እስከ መስከረም 7 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ በኢትዮ ኔትወርክ ያልተመዘገቡ የሞባይል ቀፎዎች ወይም ሌሎች በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች ከመስከረም 8 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት መስጠት አይችሉም፡፡

Comments
Post a Comment