አሜሪካ ካስፐርስኪ ሶፍትዌር ጥቅም ላይ እንዳይውል ከልክላለች

 የአሜሪካ የደህንነት ቢሮ የሩሲያ የኮምፒተር ደህንነት ኩባንያ ምርት የሆነው ካስፐርስኪ ሶፍት ዌር ጥቅም ላይ እንዳይውል አሳሰበ።
የደህንነት ቢሮው ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ኤጀንሲዎች ካስፐርስኪ የተባለውን ሶፍትዌር ከኮምፒውተራቸው ላይ እንዲያስወግዱም አሳስቧል።
እንደ ቢሮው ገለጻ፥ ከዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው በካስፐርስኪ ላብ ኩባንያ እና በሩሲያ የስለላ አገልግሎት ተቋም መካከል ያለው ግንኙነት ስላሳሰበው ነው።
የአሜሪካ የደህንነት ቢሮ ተጠባባቂ ፀሃፊ ኤላይን ዱክ፥ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ካስፐርስኪ ሶፍትዌርን ከኮምፒውተራቸው ላይ በማጥፋት በሌላ እንዲተኩ የ90 ቀን ጊዜ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።
መቀመጫውን ሩሲያ ያደረገው የካስፐርስኪ ላብ ኩባንያ ግን ከክሬምሊን መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም በሚል የሚቀርብበትን ውንጀላ እያጣጣለ ነው።
ውሳኔው እንዳሳዘነው ያስታወቀው የካስፐርስኪ ኩባንያ፥ ከሩሲያ መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እድለሌለው ለማረጋገጥ እንደሚሰራም አስታውቋል።
ሆኖም ግን ኩባንያው ላይ እየቀረበ ያለውን ውንጀላ ተከትሎም በርካታ የአሜሪካ ኩባንያዎች ካስፐርስኪን ከሽያጫቸው ውስጥ ማውጣት ጀምረዋል።
ካስፐርስኪ በዓለም ላይ ከ400 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ያሉት ሲሆን፥ ሆኖም ግን እስካሁን ለአሜሪካ መንግስት ከፍተኛው የሶፍት ዌር አቅራቢ መሆን አልቻለም።

Comments

Popular posts from this blog

የኢንተርኔት ፍጥነት መጨመሪያ መላዎች

እንዴት የስልክ ቁጥርዎን መደበቅ ይችላሉ?

የሞባይል ባትሪንእድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮች