አዲስ ቀፎ መግዛት ሲፈልጉ
አዲስ ቀፎ መግዛት ሲፈልጉ
• አዲስ የሞባይል ቀፎ ወይም ሌሎች በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች ሲገዙ በኢትዮ ኔትወርክ እንዲሰራ የተፈቀደለት መሆኑን ለማወቅ :-
• ሲም ካርድ አስገብተው ለሙከራ መጠቀም
• *868# ደውለው 3ኛ ቁጥር ላይ የሚገኘውን የመለያ ቁጥር ሁኔታ ማወቂያ (Check Status) የሚለውን መምረጥ ፤ በመቀጠል by IMEI የሚለውን መርጠው፤ ሊገዙ ያሰቡትን የቀፎ መለያ ቁጥር /IMEI/ አስገብተው ቀፎው በኢትዮ ኔትወርክ እንዲሰራ የተፈቀደለት መሆኑን ማረጋገጥ፡፡
- የሚገዙትን ቀፎ የIMEI ቁጥር ለማወቅ፡
• *#06# ይደውሉ
• ከቀፎው ማሸጊያ ካርቶን ላይ ይመልከቱ፡፡
ግዢ ከፈፀሙ በኋላ ቀፎዎ በኔትዎርኩ ላይ የማይሠራ ከሆነስ?
• ከግዢ ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን በህግ አግባብ ለመፍታት እንዲችሉ ግዢ ሲፈፅሙ የቀፎውን መለያ ቁጥር የያዘ ህጋዊ ደረሰኝ መቀበልዎን አይርሱ፡፡
ስርቆት ወይም መጥፋት ቢያጋጥምዎ?
• በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች በተለይ የሞባይል ስልክ በስርቆትም ሆነ በሌላ ምክንያት ከደንበኞች እጅ ሲጠፋ 994 ላይ ደውለው በማዘጋት ቀፎው በሌላ አካል የቴሌኮም አገልግሎት እንዳይሰጥ ማድረግ ይችላሉ፡፡

ምንጭ; ኢትዮቴሌኮም
Comments
Post a Comment