እንዴት የስልክ ቁጥርዎን መደበቅ ይችላሉ?
እንዴት የስልክ ቁጥርዎን መደበቅ ይችላሉ? ................................................................ የሞባይል ስልክ ቁጥርዎ ድብቅ እንዲሆን ይፈልጋሉ? የእርስዎ ቁጥር ድብቅ/የማይታይ እንዲሆን የሚፈልጉበት ብዙ ምክንያቶች ሊኖር ይችላሉ ፡፡ ስለዚህ እርስዎ የስልኩ ባለቤት ስለሆኑ የፈለጉትን የማድረግ መብትዎ ነው፡፡ ውጤቱ ጊዜያዊ ወይም ቋሚ ሊሆን ቢችልም ተመሳሳዩን ግብ ለማሳካት የተለያዩ መንገዶች አሉ፡፡ በዚህ በምነግራችሁ ሂደት ውስጥ በሚደውሉበት ጊዜ የስልክ ቁጥር መደበቅ ስለሆነ ሶስት የተለያዩ መንገዶችን እጠቁማለሁ የቀለለውን እና የተሻለውን የሚስማማውን መጠቀም ይችላሉ፡፡ ማሳሰቢያ: ምንም እንኳን ስደውሉ ስልክ ቁጥሩ ድብቅ ቢሆንም የድንገተኛ አደጋ ቁጥሮችእንደ 911 አይታገድም መንገድ 1: ለመደወል ቅድመ ቅጥያ ይጠቀሙ በአብዛኛው አገሮች ውስጥ ለመደወል የሚፈልጓቸውን ቁጥሮች መጀመሪያ ላይ ኮድ ማስገባት የሚያስፈልግ ሲሆን በሚደውሉበት ጊዜ ቁጥሩ በተቀባዩ ስልክ ላይ አይታይም፡፡ ኮዱ ከአገር ወደ አገር እንዲሁም የስልክ ካምፓኒዎች የሚለያይ በመሆኑ ትክክለኛውን ኮድ ማግኘት ያስፈልጋል ይሁን እንጂ በአብዛኞቹ አገሮች ቅድመ ቅጥያ ኮድ * 67፣ # 37 # እና * 37 # ይሰራል፡፡ ስለዚህ እርስዎ የሚኖሩበትን አገር እንዲሁም የያዙትን ስልክ ካምፓኒ ኮድ የማያውቁት ከሆነ እነዚህን መጀመሪያ ይሞክሩ እርስዎ ማድረግ የሚጠበቅብዎት ከመደወልዎ በፊት ከላይ ያሉትን አንዱን ኮድ አስቀድመው የሚደውሉለትን ሰው ቁጥር በመጨመር መደወል ነው፡፡ ለምሳሌ፡- * 67XXXXXXXXXX መጀመሪያ የትኛው ኮድ እንደሚሠራልዎ ይሞክሩ አስተያየትዎን ይስጡን መንገድ 2፡ በሞባይል ስልኩ ሴቲንግ ላይ ያለውን ቅንብሮ...